የኢራቅ የጦር ሰራዊት አጨቃጫቂዋ ኪርኩክ ከተማ በስተሰሜን ያለ ቁልፍ የአየር ኃይል ሰፈር እና የአውሮፕላን ጣቢያ መቆጣጠሩን ገለፀ።
ዋሺንግተን ዲሲ —
የኢራቅ የጦር ሰራዊት አጨቃጫቂዋ ኪርኩክ ከተማ በስተሰሜን ያለ ቁልፍ የአየር ኃይል ሰፈር እና የአውሮፕላን ጣቢያ መቆጣጠሩን ገለፀ።
የነዳጅ ኩባኒያና ሌሎችም ከተማዋ ዙሪያ ያሉ ይዞታዎችን ተቆጣጥረናል ብሉዋል።
ዛሬ ሰኞ የኢራቅ የፀጥታ ኃይሎች ከኩርድ ኃይሎች አስለቅቀው የአየር ኃይል ሰፈሩን የያዙት ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይደር አል አባዲ የመንግሥት ደጋፊ ኃይሎች የኪርኩክን ፀጥታ እንዲያስከብሩ ያደረጉትን ጥሪ ተከትሎ መሆኑ ታውቋል።
አባዲ ለሀገሪቱ ህዝብ ባሰሙት ንግግር “ኢራቅን የመበታተን አደጋ ላይ የሚጥል” ካሉት የኩርዶች የነጻነት ውስኔ ሕዝብ በኋላ ዕርምጃ የመውሰድ ኃላፊነት አለብን ብለዋል።