(ይህ ገፅ ሲከፈት የተደራረቡ ወይም የተረበሹ ድምፆችን የሚሰሙ ከሆነ ኮምፕዩተርዎ ከአንድ በላይ ድምፅ ማጫወቻ አለው ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ከዚህ ፅሁፍ ሥር ካሉት ማጫወቻዎች አንደኛውን ብቻ አስቀርተው ሌሎቹን ያቁሟቸው፡፡)
መንግሥት ይህንን ያስታወቀው የጠቅላይ ሚኒስትሩን የጤንነት ሁኔታ አስመልክቶ ትናንት በተዘጋጀ የመጀመሪያ ጋዜጠዊ መግለጫ ላይ ነው፡፡ ከዚህ መግለጫ በኋላም የወጣ መረጃ የለም፡፡
የጠቅላይ ሚኒስትሩን ጤንነት የተመለከቱ መረጃዎች ግን በተለያየ መንገድ ሲናፈሱ ቆይተዋል፡፡ “ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስፈላጊው የሕክምና እርዳታ ተደርጎላቸዋል፤ በአሁኑ ሰዓትም እረፍት በማድረግ ላይ ናቸው” የሚለው የትናንቱ አባባልም ለመግለጫው መዘግየት ማሣያ ነው፡፡
መረጃው ይፋ ሣይሆን መቆየቱን የተቀበሉት ሚኒስትሩ አቶ በረከት ስምዖን ይህ የመነጨው ከድርጅታቸው ኢሕአዴግና ከመንግሥት ባሕል መሆኑን ገልፀዋል፡፡
የትናንቱን የመንግሥት መግለጫ ተከትሎ የመንግሥት የመገናኛ ብዙኃን ለመጀመሪያ ጊዜ ስለጠቅላይ ሚኒስትሩ የጤንነት ሁኔታ ዘግበዋል፡፡
ዘገባውን ያዳምጡ፡፡
(ገፁ ሲከፈት የተደራረቡ ወይም የተረበሹ ድምፆችን የሚሰሙ ከሆነ ከዚህ ሥር ካሉት ማጫወቻዎች አንደኛውን ብቻ አስቀርተው ሌሎቹን ያቁሟቸውና የሚጫወተውን እንደገና ያስጀምሩት፡፡ )