በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ቡድን "ህወሓትን የማዳን" የሚል ስብሰባ ማካሄድ ጀምሯል

Your browser doesn’t support HTML5

በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ቡድን "ህወሓትን የማዳን" የሚል ስብሰባ ማካሄድ ጀምሯል

ለሁለት በተከፈለው የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ(ህወሓት) አመራር አንዱን ቡድን በሚመሩት የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ቡድን የተጠራ “ህወሓትን የማዳን” የተባለ ስብሰባ፣ ዛሬ ሰኞ፣ በመቐለ ከተማ ተጀምሯል።

ዛሬ ሰኞ፣ መስከረም 20 ቀን 2017 ዓ.ም በተጀመረው ስብሰባ ላይ የተናገሩት አቶ ጌታቸው፣ “ልዩነቱን በግልፅ ለማሳየት ያግዛል” ሲሉ ተናግረዋል።

በሌላ በኩል አቶ ጌታቸው በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ከደቡብ ምስራቃዊ ዞን ከመጡ አመራሮች ጋራ ትላንት እሁድ በመቀሌ ከተማ ውይይት ኣካሂደዋል፡፡