መቐለ ዩኒቨርሲቲ ከጦርነቱ መቆም በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ተማሪዎችን አስመረቀ

Your browser doesn’t support HTML5

መቐለ ዩኒቨርሲቲ ከጦርነቱ መቆም በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ተማሪዎችን አስመረቀ

የመቐለ ዩኒቨርሲቲ፣ የትግራይ ክልልን መነሻ አድርጎ በሰሜን ኢትዮጵያ የተካሔደው ጦርነት በሰላም ስምምነት ከቆመ በኋላ፣ የመጀመሪያ የኾነውን የተማሪዎች ምረቃ ሥነ ሥርዐት፣ ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ አከናውኗል፡፡

ዩኒቨርሲቲው በዕለቱ፣ ከመጀመሪያ ዲግሪ እስከ ድኅረ ምረቃ ሦስተኛ ዲግሪ ድረስ ትምህርታቸውን በተለያዩ መስኮች የተከታተሉ፣ ከሁለት ሺሕ በላይ ተማሪዎቹን አስመርቋል፡፡

ከሦስት ዓመታት በፊት በ2013 ዓ.ም. መመረቅ ይገባቸው የነበሩ ተማሪዎች በተካተቱበት በዚኹ የምረቃ መርሐ ግብር ላይ፣ ለአሜሪካ ድምፅ አስተያየት የሰጡ ምሩቃን፣ ከአስከፊው ጦርነት ወጥተው ለዚኽ ቀን በመብቃታቸው ከፍ ያለ ደስታ እንደተሰማቸው ተናግረዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።