የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ረዳት መምህራን ቅሬታ አሰሙ

  • ግርማይ ገብሩ

መቀሌ ዩኒቨርሲቲ

የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ባልደረቦች የሆኑ ከመቶ በላይ ረዳት መምህራን ከሁለት ዓመታት በፊት ለጠየቁት የሥራ ዕድገት መልስ እስካሁን እንዳልተሰጣቸው እየተናገሩ ነው፡፡

Your browser doesn’t support HTML5

የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ረዳት መምህራን ቅሬታ አሰሙ

የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ባልደረቦች የሆኑ ከመቶ በላይ ረዳት መምህራን ከሁለት ዓመታት በፊት ለጠየቁት የሥራ ዕድገት መልስ እስካሁን እንዳልተሰጣቸው እየተናገሩ ነው፡፡

ቅሬታ አቅራቢዎቹ “ለከፍተኛ የትምህርት ደረጃ ዕድገት እንዳንወዳደር ተደርገናል፤ በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች የሚሰጠውን የቤት ኪራይ አበልና ሌሎችም ጥቅማጥቅሞችን ተከልክለናል” ብለዋል፡፡

የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ የሥርዓተ-ትምህርት ምክትል ፕሬዚዳንት ዶ/ር አብዱልቃድር ከድር ለቪኦኤ በሰጡት ቃል “ረዳት መምህራኑ የትምህርት ደረጃ ዕድገት በውድድር እንዲሆን ሕግ ስለሚያዝ እንጂ መብታቸውን አልተከለከሉም” ብለዋል፡፡

የቤት ኪራይ አበል መከልከላቸውን አስመልክቶ መምህራኑ ላነሱት ጥያቄ ሲመልሱ “ማግኘት እንደማይችሉ በሕግ ስለተደነገገ ነው” ብለዋል፡፡

ለተጨማሪ የግርማይ ገብሩን ዘገባ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡