የኢትዮጵያ መንግሥት የአልጀርስን ስምምነትና የሄግን የድንበር ኮሚሽን ውሣኔ እንደሚቀበል ማስታወቁን በመቃወም አረና ለሉአላዊነትና ለዴሞክራሲ የጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ዛሬ መቀሌ ላይ ተካሂዷል።
መቀሌ —
የኢትዮጵያ መንግሥት የአልጀርስን ስምምነትና የሄግን የድንበር ኮሚሽን ውሣኔ እንደሚቀበል ማስታወቁን በመቃወም አረና ለሉአላዊነትና ለዴሞክራሲ የጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ዛሬ መቀሌ ላይ ተካሂዷል።
የአረና ትግራይ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አንዶም ገብረሥላሴ ለቪኦኤ በሰጡት ቃል “የኢሕአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ውሣኔ ሕገመንግሥቱን የጣሰ ነው፤ በመሆኑም በፅኑ እናወግዘዋለን” ብለዋል።
ኃላፊው “ለኢትዮጵያዊያን ሁሉ ይድረስ” ባሉት መልዕክት “ከትግራይ፣ ከኩናማና ከኢሮብ ሕዝብ ጎን ቆማችሁ ውሣኔውን ተቃወሙ” ብለዋል።
ሰልፋቸው ሕጋዊ እንደሆነ የገለፁት አቶ አንዶም የመቀሌ ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ጥበቃም ሆነ ሌሎች ድጋፎችን እንዳላደረገላቸው በመግለፅ አማርረዋል።
ለሙሉው ዘገባ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5