የመድረክ ጥምረት ወደ ግንባርነት እንዲሸጋገር ጠቅላላ ጉባኤው ወሰነ

የመድረክ መሪዎች

ከአስር ወራት በፊት መድረክ ሲመሰርት የተቀረፀው መለስተኛ ፕሮግራም ለግንባር አደረጃጀት እንዲሆን ተብሎ እንደነበርና ስድስቱም የመድረክ አባል ድርጅቶች በተናጠል በጉዳዩ ላይ የወሰዱት ውሳኔ ለትላንት በስቲያው ስምምነት ማብቃቱን የወቅቱ ሊቀመንበር አስታወቁ። ሽግግሩ ተግባራዊ እንዲሆንና ዘለቄታም እንዲኖረው ተጨማሪ ስራዎች መኖራቸውንም ሊቀመንበሩ ይናገራሉ።