Your browser doesn’t support HTML5
Your browser doesn’t support HTML5
ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማያም ደሣለኝ ትናንት በሰጡት መግለጫ ያስተላለፉትን መልዕክት የሚያዩት በሃገሪቱ ላይ የአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታ የማወጅ ያህል አድርገው መሆኑን የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ መድረክ የወቅቱ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ለቪኦኤ ገልፀዋል፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ ከኢሕአዴግ አንዳችም የተሻለ ለውጥ እንደማይጠብቁና ተስፋ መቁረጣቸውን የመላ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አቶ አዳነ ጥላሁን ተናግረዋል፡፡
ችግሩን ፓርቲው በግልፅነት መገምገሙንና የመንግሥታዊ ሥልጣንን ምንነት በመገንዘብ ላይ ያለውን አቋም ማስተካከል ለወደፊቱ ጉዞ ዕድል እንደሚከፍት መግባባት ላይ መድረሱን ቢገልፁም የመድረክና የመኢአድ መሪዎች ግን ኢሕአዴግ እራሱን በተደጋጋሚ መገምገሙንና አሁን ማድረግ ያለበት ሕዝቡን ለመተማመኛ ድምፅ መጥራትና አዲስ ምርጫ ማካሄድ መሆኑን መክረዋል፡፡
መሪዎቹ ሥርዓቱ ተበላሽቷል የሚሉባቸውን ምክንያቶች ዘርዝረዋል፡፡
የጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም የትናንት ንግግር “የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መደንገግ ነው” ብለዋል የመድረክ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ፡፡
የወልቃይት የአማራ ማንነት ጥያቄ ኮሚቴ ዋና ፀሐፊና የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊው አቶ ተሻገር ወልደሚካኤል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በወልቃይት ጉዳይ ላይ “እርስ በራሱ የሚጋጭ ንግግር ነው ያደረጉት” ብለዋል፡፡ ኮሚቴው የሄደባቸውን መንገዶችም ዘርዝረዋል፡፡
ለተጨማሪና ዝርዝር መረጃዎች የተያያዙትን የድምፅ ፋይሎች ያዳምጡ፡፡