ሞቃዲሾ ውስጥ እአአ ባለፈው ጥቅምት 14 ቀን በተፈጸመው ከባድ የቦምብ ጥቃት 358 ስዎች ተገድለው በመቶዎች የሚቆጥሩት ደግሞ በቆሰሉበት ወቅት ከዚህ ቀደም ታይቶ በማይታወቅ መልኩ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ደም ለመለገስ ወደ ሆስፒታሎች እንደጎረፎ ተገልጿል።
ዋሺንግተን ዲሲ —
ሞቃዲሾ ውስጥ እአአ ባለፈው ጥቅምት 14 ቀን በተፈጸመው ከባድ የቦምብ ጥቃት 358 ስዎች ተገድለው በመቶዎች የሚቆጥሩት ደግሞ በቆሰሉበት ወቅት ከዚህ ቀደም ታይቶ በማይታወቅ መልኩ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ደም ለመለገስ ወደ ሆስፒታሎች እንደጎረፎ ተገልጿል።
ግጭት በማይለያት ሶማልያ ባለው የመርፌ ፍርሃትና ደም ማነስ ሊይስከትል ይችላል በሚል መሰረተ ቢስ እምነት ምክንያት አብዛኞቹ ሰዎች ደም ከመስጠት ይቆጠቡ ነበር።
በዚህ ምክንያትም ሀገሪቱ ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ ለሆነ ጊዜ የደም ባንክ አልነበረም። ሆስፒታሎች ደም ለሚያስፋጋቸው በሽተኞች ደም ለመስጠት ይቸገሩ ነበር። ይሁንና እንዲህ ዓይነቱን አመለካከት ለመለወጥ የወጣት ሀኪሞች ቡድን ያደረግው ከባድ ጥረት ውጤት እንዳስገኘ በቅርቡ በተፈፀመው አስከፊ ጥቃት በተግባር ታይቷል።
በቅርቡ በሕክምና ትምህርት ከተመረቁት ሀኪሞች መካከል አንዱ ኡመር ሐቢብ ጥቃቱ ከተከሰተ በኋላ ቡድኑ ከዚህ ቀደም ደም ለመለገስ የተመዘገቡትን በማፈላለግ ለተቀረው ሕዝብም በማኅበራዊ ሚድያ ጥሪ በማድረጉ ሰዎች ደም ለመለገስ እንዲጎርፉ ማስቻሉን ጠቁሟል።