የአንበጣ መንጋ

ፎቶ ፋይል

ከሁለት ሳምንታት በፊት በባሌ ዞንጨ ተከስቶ የነበረው የአንበጣ መንጋ ወረራ በደቡብ እና ምስራቅ የኦሮምያ ክልል ዞኖች እየተስፋፋ ነው ተባለ።

እውነትም መዘግየቶች መታየታቸውን የገለፀው የኦሮምያ የእርሻ እና ተፈጥሮ ሀብት ቢሮ አሁን ቀድመ ዝግጅቶች አልቀው መንጋውን በአውሮፕላን የኬሚካል ዕርጭት ለመመልከት እንቅስቃሴ መጀመሩን አስታውቋል።

በሌላም በኩል ደቡብ ክልል የተለያዩ አከባቢዎች የበረሃ አንበጣ መንጋ መከሰቱን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ።

በክልሉ ኮንሶ ዞን፥ አማሮና ቡርጂ ልዩ ወረዳዎች የተከሰተው የአንበጣ መንጋ የተለያዩ ቋምና ጊዜያዊ ሰብሎችን ላይ ጉዳት አያደረሰ መሆኑን የአከባቢው የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች ገልፀዋል።

የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

የአንበጣ መንጋ