የኦርላንዶው ጥቃት ራሱን እስላማዊ ግዛት በሚል ከሚጠራው ጽንፈኛ ቡድን ጋር በቀጥታ የተገናኘ ስለመሆኑ እስካሁን አንዳችም ሁነኛ አመላካች ያለመኖሩን የዩናይትድ ስቴትሱ የፌድራል ምርመራ ቢሮ FBI ዲሬክተር James Comey አስታወቁ።
ዲሬክተሩ አክለውም ድርጅታቸው:- “ግለሰቡ በኢንተርኔት አማካኝነት በሚሰራጩ የሽብር መረጃዎች የአክራሪነትን አቅጣጫ ወይም ፈለግ የተከተለ ነው፤” የሚል ዕምነት እንዳለው ተናግረዋል።
ዋና መቀመጫውን በዋሽንግተን ዲሲ ያደረገው የዓለም አቀፍ ጉዳዮች ጥናት ተቋም Brookings የውጭ ፖሊሲ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ Eric Rosand በበኩላቸው በሰጡት አስተያየት፤ የእሁድ የሽብር ጥቃት፤ ለብጥብጥና ለውድመት ገቢሮች የተማረኩ እና ይልቁንም የሕይወት አቅጣጫቸው የጠፋባቸውና በቁጣ የተመሉ ወጣት ሙስሊሞች በጽንፈኛው የአሸባሪ ቡድን ISIS የሚሠራጩትን የጥፋት መልዕክቶች እንዴት እንዐሚቀበሉ የሚያሳይ ነው፤ ብለዋል።
“እነኝህም የሽብር አዝማሚያዎች አገሮች በየራሳቸው የሚዋጓቸው ዓይነቶች ናቸው፤” ሲሉም ተንታኙ አክለዋል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5