በኢትዮጵያ በየዓመቱ 2.6 ሚሊየን ሕፃናት የሚወለዱ ቢሆንም ካለፉት ዓመታት ጋር ሲነፃፀር ቁጥሩ እየቀነሰ የምጣቱን የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሥነ-ሕዝብ ጉዳይ ፅ/ቤት ከእንግሊዝ መንግሥት እንዲሁም ከቢልና ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የቤተሰብ ምጣኔ ስብሰባ ለዘርፉ ከፍተኛ ገንዘብ ያስገኛል ተብሎ ተጠብቋል፡፡
ለንደን ላይ በሚካሄደው የቤተሰብ ምጣኔ ስብሰባ ላይ የሚገኙት የጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም የኢትዮጵያን ልምድ እንደሚያካፍሉ ሚኒስትር ዴኤታው ዶ/ር ከሰተብርሃን አድማሱ ለቪኦኤ ገልፀዋል፡፡
ለዚሁ ስብሰባ ዝግጅት ሲባል አዲስ አበባ ላይ በተዘጋጀው አውደ ጥናት ላይ የተገኙት ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ከሰተብርሃን ኢትዮጵያ ከቤተሰብ ምጣኔ አንፃር መሻሻል እያሣየች መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ዝርዝሩን ከእስክንድር ፍሬው ዘገባ ያዳምጡ፡፡
(ገፁ ሲከፈት የተደራረቡ ወይም የተረበሹ ድምፆችን የሚሰሙ ከሆነ ከማጫወቻዎቹ አንደኛውን ብቻ አስቀርተው የቀሩትን ያቁሟቸው፡፡)