ድሬዳዋ —
በኢትዮጵያ የተከሰተውን የአንበጣ መንጋን ለመከላከል እስካሁን ከ700ሺ በላይ ሄክታር መሬት ላይ ርጭት መደረጉን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ። ይህም ሆኖ ግን የአንበጣ መንጋውን ለመቆጣጠር አስቸጋሪ ሆኗል ተብሏል።
የግብርና ሚኒስቴር ሚኒስትር ደኤታው ዶ/ር ማንደፍሮ ንጉሴን የኬሚካል መርጫ አውሮፕላን እጥረትን እንደ ዋና ችግር አንስተዋል። የመንግሥት ተቋማት፣ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ ሁሉም ዜጋ በሚችለው ሁሉ ርብርብ እንዲያደርግም ጠይቀዋል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5
የአንበጣ መንጋን ለመቆጣጠር አስቸጋሪ ሆኗል ተባለ