ምሥራቅ ኢትዮጵያ አጎራባች ክልሎች የአንበጣ ወረርሺኝን በጋራ ተቀናጅተው መከላከል እንዳለባቸው ተጠቆመ። የግብርና ሚኒስትሩ አቶ ዑመር ሁሴን የሶማሌ ክልልን፣ የምሥራቅና ምዕራብ ኦሮሚያን እንዲሁም የድሬዳዋ አስተዳደርን አመራሮች ሰብስበው የአንበጣ ወረርሺኝን በጋራ መከላከል በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ምክክር አድርገዋል።
በሌላ በኩል በምሥራቃዊ የአማራ አካባቢዎች በተከሰተው የበርሃ አምበጣ መንጋ ጉዳት የደረሰባቸውን አርሶ አደሮች ለማቋቋም እንደሚሰራ ግብርና ሚኒስትር ገለጸ፡፡ ሚኒስተር ዲኤታ ወንዳለ ሃብታሙ ከአሜሪካ ድምፅ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደገለጹት ከትግራይ ክልል የመረጃ አቅርቦት እጥረት ቢኖርም በአካባቢው የተከሰተውን የአምበጣ መንጋ የመከላከል ተግባር ይከናወናል ብለዋል፡፡
በተያያዘም ዜና በትግራይ ክልል የአንበጣ መንጋ ወረርሽኝ በአራት ዞኖች እና በ17 ወረዳዎች ተስፋፍቷል። የክልል የግብርና ገጠር ልማት ቢሮ እንደገለጸው፤ የአንበጣ መንጋው ለመከላከል ሰፊ ጥረት እየተደረገ ቢሆንም በአዝርእት ላይ ጉዳት አድርሷል ብሏል።
የክልሉ መንግሥት ለፌደራል መንግሥት ስለ አንበጣው ሁኔታ መረጃ አይልክም ብሎ የግብርና ሚኒስትር ስላነሳው ክስ ከቢሮው ጠይቀን፤ በየጊዜው በተለይ የአውሮፕላን ርጭት በሚያስፈልግባቸው ቦታዎች ላይ መረጃ ቢላክም የፌደራል መንግሥት ግን ትግራይን ለይቶ ሌላ አከባቢ ርጭቱን እንደሚያካሂድ ተናግረዋል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5