በሊቢያው የጎርፍ አደጋ የሟቾች ቁጥር ከአምስት ሺሕ በለጠ

  • ቪኦኤ ዜና

Your browser doesn’t support HTML5

በሊቢያው የጎርፍ አደጋ የሟቾች ቁጥር ከአምስት ሺሕ በለጠ

በሊቢያ ምሥራቃዊ የባሕር ዳርቻ ከተማዋ ዴርና፣ ሁለት ግድቦች ተደርምሰው በደረሰው የጎርፍ አደጋ የሞቱት ሰዎች ቁጥር ከ5ሺሕ100 በላይ ማሻቀቡን፣ የአገሪቱ ጤና ባለሥልጣናት ተናገሩ፡፡

ብዙ ሺሕዎች የገቡበት እንዳልታወቀና የሟቾቹ ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል፣ የምሥራቅ ሊቢያ ባለሥልጣናት ተናግረዋል፡፡ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፍልሰተኞች ጉዳይ ተቋም፣ በአደጋው ከ30ሺሕ ሰዎች በላይ ቤት አልባ እንደኾኑ አስታውቋል፡፡

የቪኦኤው ዘጋቢ ኤድዋርድ ዬራኒያን ከካይሮ ተከታዩን ዘገባ ልኳል፤ ደረጀ ደስታ ወደ ዐማርኛ መልሶታል፡፡