የሰማያዊ ፓርቲ መሪዎችና ቀስቃሾች ባሕር ዳር ላይ ታሠሩ

  • መለስካቸው አምሃ

Ethiopian Blue party Logo

የሰማያዊ ፓርቲ የብሄራዊ ምክር ቤት አባላትና ቀስቃሾች ለሕገወጥ ስብሰባ ቀስቅሳችኋል ተብለው በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የፓርቲው ምክትል ሊቀመንበር አቶ ነገሠ ተፈረደኝ ለቪኦኤ አስታወቁ፡፡

Your browser doesn’t support HTML5

የሰማያዊ ፓርቲ መሪዎችና ቀስቃሾች ባሕር ዳር ላይ ታሠሩ

የሰማያዊ ፓርቲ የብሄራዊ ምክር ቤት አባላትና ቀስቃሾች ለሕገወጥ ስብሰባ ቀስቅሳችኋል ተብለው በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የፓርቲው ምክትል ሊቀመንበር አቶ ነገሠ ተፈረደኝ ለቪኦኤ አስታወቁ፡፡

ፓርቲው ለነገ፤ ዕሁድ ሰኔ 26/2008 ዓ.ም ባሕር ዳር ከተማ ውስጥ ለማካሄድ አቅዶት ለነበረው ስብሰባ ከአስተዳደሩ ፍቃድ ማግኘታቸውን አቶ ነገሠ ገልፀዋል፡፡

ይሁን እንጂ ፖሊስ ሁለት የከተማው ነዋሪዎች የሆኑ የፓርቲውን ደጋፊዎች ጨምሮ ለስብሰባው ከአዲስ አበባ ወደ ባሕርዳር የተጓዙ የፓርቲው የብሄራዊ ምክር ቤት አባላትን በጠቅላላው አሥር ሰዎችን ማሠሩን ምክትል ሊቀመንበሩ አክለው ጠቁመዋል፡፡

የሰማያዊ ፓርቲ መሪዎችና ደጋፊዎቹ የታሠሩት ባሕር ዳር ከተማ ውስጥ ነው፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡