አውስትራልያ ውስጥ በሚገኝ አንድ የስደተኞች ማቆያ እስር ቤት ውስጥ የሰፈሩ ከ600 በላይ ጥገኝነት ጠያቂዎች፣ የአካባቢው ኗሪዎች ያስነሱብናል የሚሉትን አመፅ በመፍራት ከካምፑ ውስጥ አንወጣም ማለታቸው ተገለፀ።
አውስትራልያ ውስጥ በሚገኝ አንድ የስደተኞች ማቆያ እስር ቤት ውስጥ የሰፈሩ ከ600 በላይ ጥገኝነት ጠያቂዎች፣ የአካባቢው ኗሪዎች ያስነሱብናል የሚሉትን አመፅ በመፍራት ከካምፑ ውስጥ አንወጣም ማለታቸው ተገለፀ።
ምንም እንኳ ባለሥልጣናት የውኃና የኤሌክትሪክ አገልግልት እንደተቋረጠ ቢናገሩም፤ እስረኞቹ ግን፣ በፓሲፊክ ደሴቷ Papua New Guinea ከምትገኘው ከማኑስ ደሴት ላለመልቀቅ የወሰኑ መሆናቸውም ታውቋል።
ካምፑ ለጊዜውም ቢሆን እንዳይዘጋ ግን፣ Papua New Guinea ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጣልቃ እንዲገባ፣ የሕግ ባለሙያዎች ጥያቄ አቅርበዋል።
ጥገኝነት ጠያቂዎቹ እንዳስታወቁት ከሆነ፣ ማንነታቸው ያልታወቀ ሰዎች ወደ ማዕከሉ በመግባት፣ ወንበሮችንና ሌሎች መገልገያ ቁሳቁሶችን አውጥተው ወስደዋል።
ለጥበቃ የተቀጠሩት የደኅንነት ኃይሎችም የማኑስ ቅጥር ግቢን ለቀው መሄዳቸውን ስደተኞቹ አክለው ተናግረዋል።