ሎስ አንጀለስ ለስደተኞች ከለላ የሚሰጥ ድንጋጌ አጸደቀች

  • ቪኦኤ ዜና

Your browser doesn’t support HTML5

ሎስ አንጀለስ ለስደተኞች ከለላ የሚሰጥ ድንጋጌ አጸደቀች

በካሊፎርኒያ ግዛት የምትገኘው ሎስ አንጀለስ ከተማ ለስደተኞች ከለላ የሚሰጥ ድንጋጌ አጽድቃለች። ውሳኔው የተላለፈው፣ ተመራጩ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በጥር ወር ሥልጣን ሲረከቡ ስደተኞችን በጅምላ ወደ ሀገራቸው ለመመለስ ቃል መግባታቸውን ተከትሎ ነው።

ድንጋጌው የፌደራል ባለሥልጣናት ሕጋዊ ሰነድ የሌላቸውን ስደተኞች ከማባረር ማገድ ባይችልም፣ ከተማዋ ለስደተኛ ነዋሪዎቿ ከለላ ለመስጠት የገባችውን ቃል እንደሚያጠናክር ተገልጿል።

አንጄሊና ባግዳሳሪያን በዚህ ዙሪያ ያጠናቀረችውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።