ሳልቫ ኪር ወታደራዊ ባለሥልጣናት ላይ ተመድ ያወጣውን ዘገባ ነቀፉ

  • ቪኦኤ ዜና
ፎቶ ፋይል

ፎቶ ፋይል

ብዛት ያላቸው የደቡብ ሱዳን ወታደራዊ ባለሥልጣናት የጦርነት ወንጀሎች ፈፅመዋል ብሎ በቅርቡ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ያወጣውን ዘገባ የፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ቃል አቀባይ ነቀፉት።

ብዛት ያላቸው የደቡብ ሱዳን ወታደራዊ ባለሥልጣናት የጦርነት ወንጀሎች ፈፅመዋል ብሎ በቅርቡ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ያወጣውን ዘገባ የፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ቃል አቀባይ ነቀፉት።

አቴኒ ዌክ አቴኒ ለቪኦኤ የደቡብ ሱዳን ትኩረት ፕሮግራም በሰጡት ቃለ መጠይቅ ሪፖርቱ ሀገሪቱን ይብሱን ወደብጥብጥ የሚያመራ ብዛት ያለው ርስ በርሱ የሚጋጭ ይዘት ያለው ነው ብለዋል።

የመንግሥታቱ ድርጅት የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በቅርቡ ያወጣው ሪፖርት በጦርነት ወንጀል እና በሰብዕና ላይ በተፈፀሙ ወንጀሎች በግል ተጠያቂ የሆኑ ያላቸውን ከአርባ የሚበልጡ የደቡብ ሱዳን ከፍተኛ ወታደራዊ ባለሥልጣናት ስም ዝርዝር አውጥቷል።