የኬንያ ሙስሊሞች ክርስቲያኖችን ከአል ሻባብ ጥቃት ሸፈኑ

  • ቪኦኤ ዜና

ፎቶ - ፋይ፤ አል ሻባብ ቀደም ሲል ማንዴራ ውስጥ አድርሶት ከነበረ ጥቃት

የአልሸባብ ደጋፊዎች እንደሆኑ የሚታመን ጠብመንጃ አንጋቢዎች ባለፈው ሰኞ ከማንዴራ ወደ ናይሮቢ ያመራ የነበር የሕዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ ማገታቸው ሙስሊም እና ክርስቲያን ተሣፋሪዎችን ለመለያየት ጥረት ማድረጋቸው ተዘግቧል።

Your browser doesn’t support HTML5

የኬንያ ሙስሊሞች ክርስቲያኖችን ከአል ሻባብ ጥቃት ሸፈኑ

የአልሸባብ ደጋፊዎች እንደሆኑ የሚታመን ጠብመንጃ አንጋቢዎች ባለፈው ሰኞ ከማንዴራ ወደ ናይሮቢ ያመራ የነበር የሕዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ ማገታቸው ሙስሊም እና ክርስቲያን ተሣፋሪዎችን ለመለያየት ጥረት ማድረጋቸው ተዘግቧል።

ሙስሞቹ መንገደኞች ግን የጥቃት አድራሾቹን ትዕዛዝ አንቀበልም ብለው ክርስቲያኖቹ ለመለየት ፈቃደኛ እንዳልሆኑ ተዘግቧል፡፡

ከገደላችሁ ሁላችንንም ግደሉ ብለው አብረው ቆመዋል፡፡

ሙስሊሞቹ ሂጃብና ጥምጥሞቻቸውን ለክርስቲያኖቹ እየሰጡ ከጥቃት ለመከላከል ሞክረዋል፡፡

የናይሮቢ ነዋሪዎች ይህንን ኬንያዊያኑ ሙስሊሞች ማንዴራ አውራጃ ውስጥ የፈፀሙትን የፈፀሙትን ተግባር የጀግንነትና ኬንያዊ ምግባር ሲሉ አወድሰውታል፡፡

አል ሻባብ ባለፈውም ዓመት እዚያው ማንዴራ ውስጥ እንዲሁ አንድ የመንገደኞች አውቶቡስ ላይ ድንገተኛ አደጋ ጥለው ሙስሊም ያልሆኑ 28 ተሣፋሪዎችን ለይተው ካወጡ በኋላ ገድለዋቸዋል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡