የኬንያ መንግሥት የዳዳብ የስደተኞች ካምፕ ለመዝጋት አዘገየ

  • ቆንጂት ታየ

የዳዳብ የስደተኞች ካምፕ - ኬንያ

የኬንያ መንግሥት ግዙፉን የዳዳብ የስደተኞች ካምፕ ለመዝጋት ያደረገውን ውሣኔ በይደር ይዞታል።

በካምፑ የሚበዙት ሶማሊያውያን የሆኑ ወደ ሦስት መቶ ሺሕ የሚጠጉ ስደተኞች ተጠልለዋል። የኬንያ የሀገር አስተዳደር ሚኒስትር ፈቃደኛ የሆኑትን የመመለሱ ሂደት ግን ይቀጥላል፡፡

የኬንያ የሀገር ግዛት ሚኒስትር ጆሴፍ ኒካሰሪ ሀገራቸው የዳዳቡን የስደተኛ ካምፕ የመዝጋቱን ውሳኔ በይደር እንደያዘችው አስታውቀዋል።

በግዙፉ የስደተኛ ካምፕ በአሁኑ ወቅት ወደ ሁለት መቶ ሰማኒያ ሺሕ የሚገመቱ የሚበዙት ሶማሊያውያን ስደተኞች ይኖራሉ።

ዛሬ ሚኒስትሩ ናይሮቢ ውስጥ ለጋዜጠኞች በሰጡት ቃል የኬንያ መንግስት ዕቅዱን ያዘገየው የተመድ የስደተኞች ጉዳይ ኮሚሽነርና የሶማሊያ መንግሥት በአቀረቡለት ጥያቄ ምክንያት መሆኑን አመልክተዋል።

“መንግስት በሥድስት ወር ጊዜ ውስጥ የሶማሊያን ስደተኞች በሙሉ ወደሃገራቸው መልሶ ሲያበቃ ካምፑን ለመዝጋት ይዞት የነበረውን የጊዜ ገደብ እንዲያራዝም የቀረበለትን ጥያቄ መቀበሉን ላስታውቅ እወዳለሁ፤ ፈቃደኛ የሆኑትን የመመለሱ እንቅስቃሴ ግን ሳይስተጓጓል ይቀጥላል” ብለዋል።

ከናይሮቢ መሃመድ ዩሱፍ ያጠናቀረውን ዘገባ ቆንጂት ታየ ታቀርባለች፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

Your browser doesn’t support HTML5

የኬንያ መንግሥት የዳዳብ የስደተኞች ካምፕ ለመዝጋት አዘገየ