ኦዲንጋ ፍ/ቤት ሊሄዱ ነው

  • ቪኦኤ ዜና
ራይላ ኦዲንጋ

ራይላ ኦዲንጋ

ትናንት ውጤቱ በተነገረበት የኬንያ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ መሸነፋቸው የተገለፀው ራይላ ኦዲንጋ የምርጫውን ውጤት ባለመቀበል ለዳኛ አቤት እንደሚሉ አስታውቀዋል።

ኦዲንጋ “ሁሉንም የህግ አማራጮች” በመጠቀም የምርጫውን ውጤት በህግ እንደሚፈታተኑ አስታውቀዋል ሲል አሶሲዬትድ ፕረስ ዘግቧል።

የተቆጠረው ድምፅ ከተመዘገበው ድምፅ ሰጭ ቁጥር በላይ ማለትም 100.01% ሆኖ በመገኘቱ ውጤቱን እንደማያፀድቁ ያስታወቁ የምርጫ ኮሚሽኑ አራት ባለሥልጣኖች ትርፍ ሆኖ የታየው የተሰጠ ድምፅ ቁጥር በምርጫው የመጨረሻ ውጤት ላይ “ጉልህ ልዩነት” ሊያመጣ እንደሚችል ተናግረዋል።

በአፍሪካ የተረጋጋች ዲሞክራሲ ተደርጋ የምትታየው ኬንያ የሳምንታት ጭቅጭቅ ልታስተናግድና ምናልባትም ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ምርጫው እንደገና እንዲደረግ ሊወስን ይችላል ሲል ዜና ወኪሉ ጨምሮ ዘግቧል።