ወደሄይቲ ስለዘመቱት ፖሊሶች ኬኒያዊያን ምን ይላሉ?

  • ቪኦኤ ዜና

የኬንያ የፖሊስ ሃይል አባላት በሄይቲ ፖርት ኦ-ፕሪንስ ካረፉ በኋላ በቱሴይንት ሎቨርቸር ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አስፋልት ላይ ቆመው፤ በፖርት-አው-ፕሪንስ፣ ሄይቲ፣ እአአ ሰኔ 25/2024

  • “በገዛ ሀገራችን ሰላም ሳይኖር ፖሊሶች ወደሄይቲ መላክ ለምን አስፈለገ" ኬኒያዊያን

አራት መቶ የኬኒያ የጸጥታ አስከባሪ ፖሊሶች በዚህ ሳምንት ሄይቲ ገብተዋል። ፖሊሶቹ የተላኩት በጉልበተኛ ወሮበሎች ሁከት እየታመሰች ያለችውን የካሪቢያኗን ሀገር ለማረጋጋት እና ዲሞክራሲያዊ አስተዳደር አንዲመለስ ከሌሎች ሀገሮች ፖሊሶች ጋራ ኾነው ለመርዳት ነው፡፡ በሌላ በኩል ኬኒያ ውስጥ በቀረበው የግብር ጭማሪ ረቂቅ ሕግ የተነሳ የተቀሰቀሰው ተቃውሞ ቀጥሏል፡፡

Your browser doesn’t support HTML5

ወደሄይቲ ስለዘመቱት ፖሊሶች ኬኒያዊያን ምን ይላሉ?

ፓርላማውን በወረሩ ተቃዋሚ ሰልፈኞች እና በፖሊሶች መካከል በተፈጠረ ግጭት በርካታ ሰዎች ተገድለዋል። የቪኦኤዋ ማሪያማ ዲያሎ ከናይሮቢ ባስተላለፈችው ዘገባ እንዳለችው፣ “የሀገሪቱ መንግሥት የራሱ ሀገር ችግር ላይ እያለች ስለምን የሌላ ሀገር ሰላም ሊያስከብር ተነሳ” የሚል ጥያቄ የሚያነሱ ኬኒያውያን አሉ፡፡

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።