ኬንያ ውስጥ ዛሬ የተካሄደው የፕሬዚዳንታዊ ማጣርያ ምርጫ በፖሊሶችና በተቃዋሚዎች መካከል ግጭት አስከትሏል። ተቃዋሚዎች በሚበዙባቸው አካባቢዎች ደግሞ የምርጫ ጣብያዎች ሳይከፈቱ ቀርተዋል።
ዋሺንግተን ዲሲ —
ኬንያ ውስጥ ዛሬ የተካሄደው የፕሬዚዳንታዊ ማጣርያ ምርጫ በፖሊሶችና በተቃዋሚዎች መካከል ግጭት አስከትሏል። ተቃዋሚዎች በሚበዙባቸው አካባቢዎች ደግሞ የምርጫ ጣብያዎች ሳይከፈቱ ቀርተዋል።
የምርጫ ኮሚሽን ኃላፊ ዋፉላ ቼቡካቲ በምዕራብ ኬንያ ተቃውሚዎች በሚበረቱባቸው አራት ወረዳዎች ላይ በፀጥታ ተግዳሮቶች ምክንያት ምርጫው እስከ መጪው ቅዳሜ ድረስ እንዲዘገይ መደረጉን አስታውቀዋል።
Your browser doesn’t support HTML5
በኬንያ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ በፖሊሶችና በተቃዋሚዎች መካከል ግጭት ተፈጠረ
ኪሱሙ ላይ በፖሊሶችና በተቃዋሚዎች መካከል በተነሳ ግጭት አንድ ሰው በተኩስ መገደሉን ፖሊሶች ገልፀዋል። በርካታ የኪሱሙ የምርጫ ጣብያዎች ተዘግተዋል። የምርጫ ባለሥልጣኖችም ሊገኙ አልቻሉም።
ናይሮቢ በሚገኘው ደሳሳ ሰፈር ኪቤራ ተቃዋሚዎች በምርጫ ጣብያው ፊት መሰናክል ለመሥራት ሲሞክሩ ፖሊሶች ዕምባ አስመጪ ጋዝ ተኩሰውባቸዋል።