ዛሬ ነሐሴ 2/2009 ዓ.ም የሚካሄደው አምስተኛው ፕሬዝዳንታዊ የኬንያ ምርጫ ውጥረት ናይሮቢ ለሚገኙ ስደተኞች ከፍተኛ የስጋት ምንጭ እንደሆነባቸው ተናገሩ። የተጋጋለው የቅድመ ምርጫ ሂደት እርስ በእርስ ግጭት ያመጣል እንዲህ ያለ ነገር ደግሞ ለዝርፊያ፣ለመታሰር እና ለአካል ጥቃት ያጋልጣል የሚል ከፍተኛ ስጋት እንዳሳደረባቸው ወደ ሦስተኛ ሀገር ለመሻገር በመጠባበቅ ላይ ያሉ ስደተኞች ገለጹ።
ዋሽንግተን ዲሲ —
ቀድሞውንም ቢሆን ስጋት ላይ እንደነበሩ የገለጹልን ስደተኞቹ በአፍሪካ ምርጫ በሰላም አለማከናወን እንደባህል እየተቆጠረ ነው ብለዋል።
ዘገባውን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5
የኬንያ ምርጫና የኢትዮጵያውን ስደተኞች ስጋት