የኬንያ ዶክተሮች ከመንግሥት ጋራ በመስማማታቸው አድማቸውን አቆሙ

  • ቪኦኤ ዜና

Your browser doesn’t support HTML5

የኬንያ ዶክተሮች ከመንግሥት ጋራ በመስማማታቸው አድማቸውን አቆሙ

የኬንያ ዶክተሮች ውዝፍ ደሞዛቸው እንዲከፈላቸው እና ተለማማጅ ዶክተሮች እንዲቀጠሩ በመጠየቅ ለስምንት ሳምንታት ካደረጉት የሥራ ማቆም አድማ በኋላ ወደ ሥራ ለመመለስ ተስማምተዋል። መንግሥት እና የዶክተሮች ማኅበር ትላንት ረቡዕ ወደ ሥራ የመመለሻ ስምምነት የተፈራረሙ ሲሆን፣ ይህ ስምምነት በሕዝብ ሆስፒታሎች መታከም ላልቻሉ ህሙማን እፎይታ የሚሰጥ ነው።

መሀመድ ዩሱፍ ተከታዩን ዘግቧል፤ ደረጀ ደስታ ወደ አማርኛ መልሶታል፡፡