ቻይና ዩናይትድ ስቴትስን አስጠነቀቀች

  • ቪኦኤ ዜና

ፎቶ ፋይል

ከሩስያ ላይ የጦር መሳሪያ በመግዛታችን ዩናይትድ ስቴትስ በወታደራዊ ተቋማችን ላይ የጣለችውን ማዕቀብ ታንሳ አለዚያ መዘዝ ይከተላል ስትል ቻይና አሳሰበች።

ከሩስያ ላይ የጦር መሳሪያ በመግዛታችን ዩናይትድ ስቴትስ በወታደራዊ ተቋማችን ላይ የጣለችውን ማዕቀብ ታንሳ አለዚያ መዘዝ ይከተላል ስትል ቻይና አሳሰበች።

የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጌንግ ሹዋንግ ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት ቃል ሃገራቸው ስለማዕቀቡ ተቃውሞዋን በይፋ ለዩናትድ ስቴትስ አቅርባለች ብለዋል።

ዩናይትድ ስቴትስ ማዕቀቡን በመጣልዋ የዓለምቀፍ ግንኙነት መርሆችን ጥሳለች ሁለቱ ሀገሮች መንግስታት እና ጦር ሃይሎች ግንኙነትም በእጅጉ ጎድታለች ሲሉ ቃል አቀባዩ ተናግረዋል።

ዩናይትድ ስቴትስ በቻይናው ወታደራዊ ተቋም ላይ ትናንት ሃሙስ ማዕቀቡን የጣለውችው ግዢው በሩስያ ላይ የደነገገነውን ማዕቀብ የሚጥስ ነው በማለት ወንጅላ ነው።