ቱርክ ኢስታንቡል ሳውዲ ዓረብያ ውስጥ የተገደለውን ጋዜጠኛ ዣማል ኻሾግዢ አስከሬን በቀላሉ ለማስወገድ እንዲመቻቸው ቆራርጠው ወደፈሳሽነት ቀይረውታል ሲሉ አንድ የቱርክ ፕሬዚዳንት አማካሪና የሟቹ ጋዜጠኛ ጓደኛ መናገራቸውን የቱርኩ ሃሪየት ጋዜጣ ዘገበ፡፡
ዋሺንግተን ዲሲ —
ቱርክ ኢስታንቡል ሳውዲ ዓረብያ ውስጥ የተገደለውን ጋዜጠኛ ዣማል ኻሾግዢ አስከሬን በቀላሉ ለማስወገድ እንዲመቻቸው ቆራርጠው ወደፈሳሽነት ቀይረውታል ሲሉ አንድ የቱርክ ፕሬዚዳንት አማካሪና የሟቹ ጋዜጠኛ ጓደኛ መናገራቸውን የቱርኩ ሃሪየት ጋዜጣ ዘገበ፡፡
“በደረሰን መረጃ መሰረት አስከሬኑን ከማስወገዳቸው በፊት “ቆራርጠው ወደፈሳሽነት ቀይረውታል” ሲሉ ያሲን አክታይ ለጋዜጣው ተናግረዋል።
የሳዑዲ መንግሥት ጋዜጠኛው በኢስታንቡሉ ቆንስላው ውስጥ መገደሉን ሲያስተባብል ቆይቶ በኋላ ደግሞ ታቅዶ ሳይሆን በአፈንጋጭ ጋጠወጦች እጅ በድንገት ህይወቱ ጠፍቷል የሚል ማብራሪያ አስከትሏል።
ባለፈው ሳምንት ደግሞ የሳዑዲ አቃቤ ህግ ሳኡድ አል ሞጄብ ግድያው ሆን ተብሎ በዕቅድ የተፈፀመ እንደሆነ ተናግረዋል።