ፖሊስ ጋዜጠኛውን በቁጥጥር ስር ያዋለው “ሰው እየሞተ እንዴት ችግኝ ይተከላል” የሚል የቅስቀሳ ይዘት ያለው መልዕክት በማኅበራዊ ገፁ ላይ አስተላልፏል በሚል ጠርጥሮት እንደሆነ ለፍርድ ቤት ማስረዳቱን ጠበቃው አቶ መሰረት የኔሁን ለቪኦኤ ገልጸዋል፡፡
ፖሊስ ለተጨማሪ ምርመራ የ14 ቀን ጊዜ የጠየቀ ቢሆንም፣ ፍርድ ቤት በዋስትና እንዲወጣ ትዕዛዝ መስጠቱንም ጠበቃው ተናግረዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት፣ አልዓዛር በ5 ሺህ ብር እንዲፈታ የስር ፍርድ ቤቱ የሰጠውን ውሳኔ ቢያጸናም፣ የዋስትናውን ገንዘብ ማስያዛቸውን የገለጹት ቤተሰቦቹ እና ባልደረቦቹ ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት እስከምሽቱ 1፡30 ድረስ ጋዜጠኛው እንዳልተለቀቀ አረጋግጠዋል፡፡ ላለመለቀቁ በፖሊስ የቀረበው ምክንያት “ክፍለ ከተማው ይፈልገዋል” የሚል እንደሆነ ገልፀዋል፡፡
/ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/
Your browser doesn’t support HTML5