በአንድ የአማን ፖሊስ ባልደረባ ሁለት አሜሪካውያንና አንድ ደቡብ አፍሪቃዊ ተገደሉ

አንድ የቀድሞ የዮርዳኖስ ፖሊስ ባደረሰው ጥቃት ሁለት አሜሪካውያን ወታደራዊ አሰልጣኞችና አንድ ደቡብ አፍሪቃዊ ሲገድሉ ሌሎች ስድስት ሰዎች ቆስለዋል።

አንድ የቀድሞ የዮርዳኖስ ፖሊስ ባደረሰው ጥቃት ሁለት አሜሪካውያን ወታደራዊ አሰልጣኞችና አንድ ደቡብ አፍሪቃዊ ሲገድሉ ሌሎች ስድስት ሰዎች ቆስለዋል።

ከዋና ከተማይቱ አማን ወጣ ብሎ በሚገኝ የፖሊስ ማሰልኛ ካምፕ የደረሰውን ይህን መሰል ጥቃት በዮርዳኖስ ሲፈጸም የመጀመሪያው ነው።

የዛሬው የጅምላ ግድያ ዜና የተሰማው የአረብና ምዕራባውያን መንግስታት፤ አይስልንና (ISIL) ሌሎች የቡድኑ ሃጋር የሆኑ እስላማዊውን ጽንፈኞችን እየተዋጉ ባሉበትና የመካከለኛው ምሥራቅ ከፍተኛ ውጥረት በነገሰበት ባሁኑ ወቅት ነው።

የንጉስ አብዱላ ልዩ ወታደራዊ ማዕከል በመባል የሚታወቀው ይህ ወታደራዊ ማሰልጠኛ የኢራቅና የፍልስጤማውያን ኃይሎችን ለማሰልጠኛነትም የዋለ ነው።

በመካከለኛው ምሥራቅ የዩናይትድ ስቴትስ የቅርብ አጋር የሆነችው ዮርዳኖስ ካለፈው ዓመት አንስቶ በኢራቅና በሶሪያ በእስላማዊው ጽንፈኞች ላይ በሚካሄደው አሜሪካ መራሹ ወታደራዊ ዘመቻ በመሳተፍ ላይ ትገኛለች። የዩናይትድ ስቴትስና የዮርዳኖስ F-16 ተዋጊ አውሮፕላኖች ከተለያዩ የአገሪቱ የጦር ሠፈሮች በመነሳት በጽንፈኛው ቡድን አይስል (ISIL) ይዞታዎች ላይ የዓየር ድብደባዎችን ያደርጋሉ።

ሙሉውን ዝርዝር አሉላ ከበደ አቅርቦታል ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያዳምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

በአንድ የአማን ፖሊስ ባልደረባ ሁለት አሜሪካውያንና አንድ ደቡብ አፍሪቃዊ ተገደሉ