የጅማ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ

  • ቆንጂት ታየ
የጅማ ዩኒቨርስቲ ኪቶ ፉርዲሳ ግቢ ትናንት ማታ ከአምስት ሰዓት እስከ ሠባት ሰዓት ሰልፍ ያደረጉት ተማሪዎች አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ሥራ ላይ ከዋለ ወዲህ የፀጥታ ኃይሎች ሌሊት ሌሊት እየገቡ ተማሪዎች ይወስዳሉ፡፡

“እስካሁን የወሰዱዋቸውን የት እንዳደረሱዋቸው አናውቅም” ብለዋል፡፡ ለደህንነታቸው ሲሉ ስማቸውን መግለፅ ያልፈለጉት ተማሪዎች

ከዩኒቨርስቲው ዋናው ግቢ ዶክተር ፍቃዱ አሰፋ የሚባሉ መምህር ተወስደዋል ብለዋል ።

ስለሁኔታው ለመጠየቅ የጅማ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚደንት ፕሮፌሰር ፍቅሬ ለሜሳ ቢሮ ተደውሎ ስብሰባ ላይ መሆናቸው ተገልጿል።

ሆኖም የኪቶ ፉርዲሳ ግቢ የተማሪዎች ዲን የሆኑት አቶ ከማል ቱሬ ተማሪዎቹ ጥያቄዎች ማቅረባቸውን አረጋግጠዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

Your browser doesn’t support HTML5

የጅማ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ