የጃፓን ጠ/ሚ/ር በሩሲያ ጋዝ ጥገኛ ላለመሆን ኒዮክለር ምንጭ እንጠቀማለን አሉ

የጃፓን ጠ/ሚኒስትር ፉሚዮ ኪሺዳ

የጃፓን ጠ/ሚኒስትር ፉሚዮ ኪሺዳ

የጃፓን ጠ/ሚኒስትር ፉሚዮ ኪሺዳ ጃፓንም ሆነ ሌሎች አገሮች በሩሲያ የኃይል አቅርቦት ላይ ጥገኛ እንዳይሆኑ የኒዮክለር ማመንጫዎችን እንደትጠቀም ዛሬ ሀሙስ በሰጡት መግለጫ አስታወቁ፡፡

ጃፓን እኤአ በ2011 በደረሰው የርዕድ መሬትና ሱናሚ በፉኩሺማ ውድመት ከደረሰ ጊዜ አንስቶ፣ የኒዮክሊየር ማመንጫዋን በመዝጋት የሩሲያን ጋዝ መጠቀም መጀመሯ ይታወሳል፡፡

ይሁን እንጂ የተወደደውን የኃይል ምንጭ ዋጋ ጭምር ተጠቅመው፣ ባለፈው ሀምሌ በተደረገው ምርጫ ያሸነፉት፣ ኪሺዳ የአገራቸው የወደፊቱ ተስፋ ኒዮክለር ኃይል መሆኑን ተናግረው እንደነበር ተገልጿል፡፡