የቀድሞ የቻድ ፕሬዚዳንት ሞቱ

  • ቪኦኤ ዜና
የቀድሞ ፣ የቻድ ፕሬዚዳንት ሂሴኔ ሃብሬ

የቀድሞ ፣ የቻድ ፕሬዚዳንት ሂሴኔ ሃብሬ

የቀድሞ ፣ የቻድ ፕሬዚዳንት ሂሴኔ ሃብሬ ዛሬ መሞታቸውን የሴኔጋል ባለሥልጣናት አስታውቀዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ ህይወታቸው ያለፈው በሰብአዊነት ላይ በፈጸሙት የጦር ወንጀለኝነት፣ ተከሰው በተረፈደባቸው የእድሜ ልክ እስራት፣ ከነበሩበት እስር ቤት መሆኑን ተነግሯል፡፡

ሄብሬ እኤአ ከ1982 እስከ 1990 በነበረው የሥልጣን ዘመናቸው፣ ከ40ሺ ሰዎች በላይ መግደላቸውና፣ ሌሎች 200ሺ ሰዎችን ደግሞ ማሰቃየታቸው ተመስክሮባቸዋል፡፡

ሄብሬ በቅርቡ ለኮረና ቫይረስ ህክምና ከስር ተለቀው እንደነበሩ አንዳንድ መረጃዎች ጠቁመዋል፡፡

ሂስኔ ሃብሬ የ79 ዓመት ሰው እንደነበሩም ተመልክቷል፡፡