ጣሊያን ወደ አገሯ የሚጎርፈውን ፍልሰተኛ መከላከል የሚያግዝ ዐዲስ ዘዴ ሥራ ላይ ልታውል ነው

  • ቪኦኤ ዜና

ፎቶ ፋይል፦ ከሰሃራ በታች ካሉ የአፍሪካ ሀገሮች የመጡ ፍልሰተኞች ወደ ኢጣሊያ ለመድረስ ሲሞክሩ በቱኒዚያ የባህር ኃይል ብሄራዊ ጥበቃ እየታዩ ቱኒዚያ በኤስፋክስ የባህር ዳርቻ አቅራቢያ

የጣሊያን መንግሥት በልማት ላይ ያተኮረ ዐዲስ ፕሮግራም ተግባር ላይ በማዋል ስደተኞች ከአፍሪካ ተነስተው የሜዲትራኒያንን ባህር ለመሻገር የሚያደጉትን ጉዞ ለመከላከል እየሞከረ ነው። ተንታኞች እንደሚሉት እቅዱ ከሠራም መላው አውሮፓ በጥሩ ምሳሌነት ሊጠቀምበት የሚችል ነው።

Your browser doesn’t support HTML5

ጣሊያን ወደ አገሯ የሚጎርፈውን ፍልሰተኛ መከላከል የሚያግዝ ዐዲስ ዘዴ ሥራ ላይ ልታውል ነው

ሄንሪ ዊልከንስ ከጣሊያኗ የላምፔዱሳ ደሴት ለአሜሪካ ድምጻ ባጠናቀረው ዘገባ ባለፈው ዓመት በአንዲት ሳምንት ዕድሜ ብቻ በሺዎች የሚቆጠሩ ፍልሰተኞች ባሕሩን አቋርጠው እዚያ ሲደረሱ ያዩ የአካባቢው ነዋሪዎችም አዲሱን ርምጃ በይሁንታ መቀበላቸውን እየገለጹ ነው።