እስራኤል ሌሊቱን በጋዛ ሰርጥ የአየር ድብድባ አካሄደች

  • ቪኦኤ ዜና
እስራኤል ሌሊቱን በጋዛ ሰርጥ የአየር ድብድባ አካሂዳለች። የፍልስጤማዊያን ታጣቂዎች በበኩላቸው ወደእስራኤል ግዛቶች ሮኬት ተኩሰዋል።

እስራኤል ሌሊቱን በጋዛ ሰርጥ የአየር ድብድባ አካሂዳለች። የፍልስጤማዊያን ታጣቂዎች በበኩላቸው ወደእስራኤል ግዛቶች ሮኬት ተኩሰዋል።

በሁኔታው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የመካከለኛው ምሥራቅ ልዩ ልዑክ ስጋታቸውን ገልፀዋል።

የተመድ የመካከለኛው ምሥራቅ የሰላም ሂደት አስተባባሪ ኒኮላይ ምሊዴኖቭ አሁን እየተጋጋለ ያለውን ሁኔታ መቆጣጠር ካልተቻለ አጠቃላዩን ህዝብ ለከባድ ጉዳት የሚያጋልጥ ደረጃ ላይ ሊደረስ ይችላል ሲሉ አስጠንቅቀዋል።