እሥራኤል የሚገኙ 40ሺሕ ፍልሰተኞች እንዲባረሩ ተወሰነ

  • ቪኦኤ ዜና

ፎቶ ፋይል፡-ኤርትራውያን ፍልሰተኞች

እሥራኤል ውስጥ የሚገኙ 40ሺሕ ፍልሰተኞች፣ የሀገሪቱ ምክር ቤት አባሎች እንዲባረሩ በመወሰናቸው፣ መፃዒ ዕድላቸው ምን ሊሆን እንደሚች የታወቀ ነገር እንደሌለ ተሰማ።

እሥራኤል ውስጥ የሚገኙ 40ሺሕ ፍልሰተኞች፣ የሀገሪቱ ምክር ቤት አባሎች እንዲባረሩ በመወሰናቸው፣ መፃዒ ዕድላቸው ምን ሊሆን እንደሚች የታወቀ ነገር እንደሌለ ተሰማ።

ገለልተኛ ሥፍራ የሚገኘውና በብዙ ሺህዎች ለሚቆጠሩ አፍሪካውያን ሥደተኞች መጠለያ የነበረው የኔጌቨ በረሃው ሆሎት ካምፕ ሙሉ በሙሉ እንዲዘጋ፣ ኢየሩሳሌም የሚገኘው ካቢኔ ትናንት እሑድ በአንድ ድምፅ መወሰኑ ታውቋል።

በዚሁ ውሳኔ መሠረት ማዕከሉ በመጪዎቹ ሦስት ወራት የሚዘጋ ሲሆን፣ ፍልሰተኞች ለጊዜው ያላቸው አማራጭ ወይ እሥር ቤት መግባት፣ አልያም መጠለያውን ለቆ ከሀገሪቱ መውጣት ሆኗል።

አብዛኛዎቹ አፍሪካውያን ፍልሰተኞች፣ በጦርነት ከደቀቁት ኤሪትራና ሱዳን ሲሆኑ፣ በግብጹ ሲናይ በረሀ አቋርጠው ወደ እሥራኤል የገቡትም እአአ ከ2006 እስከ 2013 እንደሆነም ታውቋል።

ፍልሰተኞቹ ራሳቸውን የሚገልጹት፣ የፖለቲካ ስደተኞች እንደሆኑና ከለላም እንደሚሹ ሲሆን፣ እሥራኤል ግን አብዛኛዎቹ የኤኮኖሚ ጥገኞችና ሰርጎ ገቦች አድርጋ ነው የምታያቸው።