እስራኤል የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሐማስ ለሚጠቅምባቸው ስልቶች “ተባባሪ አጋር ነው” ስትል በመክሰስ፣ ካሁን በኋላ ለድርጅቱ ሠራተኞች እንደተጠየቀ ወዲያውኑ ቪዛ መስጠት ማቋሟን ትናንት ማክሰኞ አስታውቃለች፡፡
ርምጃው እስራኤል ከረጅም ጊዜ ጀምሮ በቀጥታ ፍትሃዊና ተመጣጣኝ ያልሆነ ትችት ይሰነዝርብኛል ስትል በምትከሰው ዓለም አቀፉ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እና በእስራኤል መካከል ያለውን አለመግባባት እንደሚያባብስ ተመልክቷል፡፡
የመንግስት ቃል አቀባይ ኤይሎን ሌቪ እንደተናገሩት እስራኤል ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሠራተኞች የሚቀርቡትን የቪዛ ጥያቄዎች እንደመጣ በጥቅሉ ወዲያውኑ ከማየት ይልቅ እንደየጉዳዩ የምታስተናግድ ይሆናል፡፡
ቃል አቀባዩ “ከሆስፒታሎች እየተንቀሳቀሱ ይዋጋሉ ፣ በጋዛ ውስጥ ለሲቪሎች የታሰበውን ዕርዳታ ይዘርፋሉ “ ያሏቸውን ታጣቂዎች ማውገዝ አልቻለም” ያሉትን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት፣ ለሐማስ “ሽፋን እየሰጠ ነው” ሲሉ ከሰዋል፡፡
ሐማስ ሁለቱንም ክሶች ውድቅ አድርጓል።