እስራኤል አራት ወታደሮቿ በሂዝቦላ ድሮን መገደላቸውን አስታወቀች

የሂዝቦላ ሰው አልባ አውሮፕላን (ድሮን) በእስራኤል ጦር ሠፈር ላይ ትላንት እሁድ ምሽት በፈጸመው ጥቃት አራት ወታደሮቹ ሲሞቱ ሰባት ሰዎች ደግሞ ክፉኛ መቁሰላቸውን የእስራኤል ጦር አስታወቀ፡፡

የሂዝቦላ ሰው አልባ አውሮፕላን (ድሮን) በእስራኤል ጦር ሠፈር ላይ ትላንት እሁድ ምሽት በፈጸመው ጥቃት አራት ወታደሮቹ ሲሞቱ ሰባት ሰዎች ደግሞ ክፉኛ መቁሰላቸውን የእስራኤል ጦር አስታወቀ፡፡

እስራኤል ሊባኖስ ላይ ካካሄደቸው ሁለት ሳምንት ከተቃረበው የእግረኛ ጦር ወረራ ወዲህ በሂዝቦላ የተፈጸመ አስከፊው ጥቃት ነው ተብሏል፡፡

ሂዝቦላህ ለጥቃቱ ኃላፊነቱን የወሰደ ሲሆን ባላፈው ሀሙስ ቤይሩት ውስጥ 22 ሰዎችን ለገደለው የእስራኤል የአየር ጥቃት አፀፋ ነው ሲል ገልጿል፡፡

እስራኤል እና ሂዝቦላህ በየቀኑ ማለት በሚያስችል መልኩ የተኩስ ልውውጥ እያደረጉ ሲሆን የጋዛ ጦርነት ከጀመረ ካለፈው አንድ ዓመት ወዲህ ውጊያው ተባብሶ ቀጥሏል፡፡