እስራኤል በሌባኖስ ባደረሰችው የአየር ጥቃት 21 ሞቱ

እስራኤል በሌባኖስ በርካታ ቦታዎች ባደረገችው የአየር ድብደባ ቢያንስ 21 ሰዎች መሞታቸውን የአሶስዬትድ ፕረስ ዘገባ አመልክቷል።

እስራኤል በሌባኖስ በርካታ ቦታዎች ባደረገችው የአየር ድብደባ ቢያንስ 21 ሰዎች መሞታቸውን የአሶስዬትድ ፕረስ ዘገባ አመልክቷል።

በደቡብ ሌባኖስ በእስራኤል ድብደባ ከተገደሉት ውስጥ የከተማዋ ከንቲባ እንደሚገኙበት ታውቋል። ድብደባው የዕርዳታ ሥራዎችን ለማስተባበር የተሰየመ ስብሰባ ላይ የነበሩ ሰዎችን መምታቱን የሌባኖስ ባለሥልጣናት አስታውቀዋል።

እስራኤል በማዘጋጃ ቤቱ ሲካሄድ የበረውንና በዕርዳታ ማስተባበር ላይ ያተኮረውን ስብሰባ “ሆን ብላ ኢላማ አድርጋለች” ሲሉ የሌባኖስ ጊዜያዊ ጠቅላይ ሚኒስትር ናጂብ ሚካቲ ክስ አሰምተዋል።

ትላንት ምሽት ደቡባዊዋን የቃና ከተማ የመታውን የአየር ድብደባ በተመለከተ እስራኤል ያለችው የለም።

እ.አ.አ በ1996፣ ከ28 ዓመታት በፊት፣ እስራኤል በቃና ከተማ በሚገኝ የተባበሩት መንግስታት ቅጥር ግቢ ላይ በፈጸመችው የከባድ መሣሪያ ድብደባ የተ መ ድ የሠላም አስከባሪ ኃይሎችን ጨምሮ ቢያንስ 100 የሚሆኑ ሰዎች ተገድለዋል። በርካቶችም ቆስለዋል።