በእስራኤል የሐማስ ታጋቾች ቤተሰቦች ሰልፍ እየወጡ ነው

  • ቪኦኤ ዜና

Your browser doesn’t support HTML5

በእስራኤል የሐማስ ታጋቾች ቤተሰቦች ሰልፍ እየወጡ ነው

በጋዛ፣ በሐማስ ታጣቂ ቁጥጥር ሥር እንደዋሉ የታመኑ፣ ወደ 240 የሚደርሱ የታጋቾች ቤተሰቦች፣ ከቴል አቪቭ ወደ ኢየሩሳሌም የሚያደርጉትን የአምስት ቀናት ጉዞ ጀምረዋል።

ቤተሰቦቹ፣ ወዳጅ ዘመዶቻቸው ነጻነታቸውን እንዲያገኙ፣ መንግሥት የበለጠ መሥራት እንዳለበት አመልክተዋል።

የሚወዷቸው ታጋች ቤተሰቦቻቸው፣ በሕይወት ስለመኖራቸው ምንም ወሬ ሳይሰሙ ሳምንታት በማለፉ፣ ለታጋቾቹ ወዳጅ ዘመዶች የሳምንታት ሥቃይ እንደኾናቸው ይናገራሉ።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡