ብሊንከን ግብፅ ናቸው

  • ቪኦኤ ዜና

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንክን ግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሜህ ሹክሪ ጋር ተገናኝተዋል፤ ካይሮ፣ ግብፅ እአአ መጋቢት

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንክን ዛሬ ሐሙስ ግብፅ ጉብኝት ላይ ናቸው፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ የግብፅ ጉዞ ትኩረት በእስራኤል እና በሃማስ መካከል ጋዛ ላይ የሚካሄደው ጦርነት ተኩስ አቁም እንዲደረግ ጋዛ ውስጥ ያሉት ታጋቾች እንዲለቀቁ እና ወደ ጋዛ ተጨማሪ የሰብዓዊ ረድዔት መግባት በሚችልበት መንገድ ዙሪያ ለመወያየት መሆኑ ተመልክቷል፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው ብሊንከን ከግብፅ ፕሬዚደንት አብደልፋታህ ኤል ሲሲ ጋር ውጊያው ቢያንስ ለስድስት ሳምንታት ያህል እንዲቆም የተቀሩት ታጋቾች በሙሉ እንዲለቀቁ ማድረግ ስለሚቻልበት መንገድ ተወያይተዋል፡፡ ከፍተኛው የዩናይትድ ስቴትስ ዲፕሎማት በመቀጠል ከዮርዳኖስ፣ ከሳዑዲ አረቢያ፣ ከካታር እና ከተባበሩት የአረብ ኤሚሬቶች ተወካዮች ጋር ይወያያሉ፡፡

በርካታ ሀገሮች እስራኤል እና ታጣቂው ቡድን ሃማስ ሁለቱም የሚቀበሉት ሃሳብ ለማቅረብ በርካታ ሀገሮች የተሳተፉበት ድርድር ለሳምንታት ሲካሄድ ሰንብቷል፡፡ ሚኒስትር ብሊንከን ነገ ዓርብ ወደእስራኤል ይጓዛሉ፡፡

ብሊንከን በእስራኤል በሚያደጉት ቆይታ “ራፋህን ጨምሮ ሃማስን ማሸነፍ የሲቪሎችን ደህንነት በሚያስጠብቅ እና የሰብዓዊ ረድዔት አቅርቦትን በማያደናቅፍ ብሎም የእስራኤልን አጠቃላይ ደህንነት በይበልጥ በሚያስጠብቅ መንገድ መከናወኑን ማረጋገጥ እንደሚነጋገሩበት ከውጭ ጉዳይ ሚንስቴር የወጣው መግለጫ አመልክቷል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ የዩናይትድ ስቴትስ የመከላከያ ሚንስትር ሎይድ ኦስተን ትናንት ከእስራኤል አቻቸው ዮአቭ ጋላንት ጋር የተነጋገሩ ሲሆን ራፋህ ላይ በየብስ ከባድ ጥቃት ከመክፈት የሚሻል አማራጮችን መፈለግ እንደሚገባ ያሳሰቧቸው መሆኑን የመከላከያ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ብሊንከን የመካከለኛው ምስራቅ ጉብኝታቸውን ትናንት በሳዑዲ አረቢያ የጀመሩ ሲሆን ከልዑል አልጋ ወራሹ መሐመድ ቢን ሳልማን እና ከውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ ፋይሳል ቢን ፋርሀን ጋር ተወያይተዋል፡፡ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጫው እንዳለው የጋዛን ሲቪሎች ደህንነት መጥበቅ እና ሰብዓዊ ረድኤቱን ከፍ ማድረግ ባስቸኳይ የሚያስፈልግ መሆኑን ተነጋግረውበታል፡፡

ሳዑዲ አረቢያ በጋዛ ሰርጥ የሚደርገውን የሰብዓዊ ረዲኤት ጥረት ለማገዝ በሚል 40 ሚሊዮን ዶላር ለተመድ የፍልስጤም ስደተኞች ጉዳይ ቢሮ ለግሳለች፡፡

ጋዛ ውስጥ የሚካሄደው ግጭት ዛሬም ቀጥሏል፡፡ እስራኤል ጋዛ ከተማ በሚገኘው ሺፋ ሆስፒታል አካባቢ በአየር እና በየብስ ጥቃትእያካሄደች መሆኗን አስታውቃለች፡፡ ትናንት ረቡዕ ኃይሎቻችን ከ50 የሚበልጡ ታጣቂዎችን ገድለዋል ሲል የእስራኤል የጦር ኃይል አስታውቋል፡፡ በደቡባዊ ጋዛ ሰርጥ ካን ዩኒስ አካባቢም ውጊያው እንደቀጠለ መሆኑ ተመልክቷል፡፡