በእስራኤል ወታደሮች ድንገተኛ ወረራ ፍልስጤማዊው ተገደለ

  • ቪኦኤ ዜና

ፍልስጤማውያን በዌስት ባንክ በሚገኘው የስደተኞች ካምፕ ውስጥ የእስራኤል ወታደሮች ባደረጉት ድንገተኛ ጥቃት ጉዳት የደረሰበት ተሽከርካሪ

እስራኤል በኃይል በያዘችው ዌስት ባንክ ውስጥ የእስራኤል ወታደሮች ባደረጉት ድንገተኛ ጥቃት አንድ የ19 ዓመት ፍልስጤማዊ መገደሉን የፍልስጤም ጤና ባለሥልጣናት አስታወቁ፡፡ ድንገተኛው ወረራ የተካሄደው ኢያሪኮ ከተማ አቅራቢያ በሚገኘው በአግባር ጃባር የመጠለያ ካምፕ ውስጥ መሆኑ ተነግሯል፡፡

የእስራኤል ጦር፣ ወታደሮቹ የተኮሱት ፍልስጤማውያኑ ተቀጣጣይ ነገሮችን ወደ ወታደሮቹ ሲወረውሩ ነው ብሏል፡፡

የፍልስጤም ጤና ሚኒስቴር ካለፈው ማክሰኞ ጀምሮ ከእስራኤል ኃይሎች ጋር በተፈጠረ ግጭት የሞቱት ፍልስጤማውያን ቁጥር ስድስት መድረሱን አስታውቋል፡፡