ፓኪስታን ውስጥ የሚገኙ እስላማዊ አክራሪዎች፣ በአናሳ ሥደተኞች የአህማዲ ማኅበረሰብ ይዞታ የሆነን አንድ የአምልኮ ሥፍራና አጠገቡ የሚገኙ የመኖሪያ ሰፈሮችን ማውደማቸው ተገለፀ።
ዋሺንግተን ዲሲ —
ፓኪስታን ውስጥ የሚገኙ እስላማዊ አክራሪዎች፣ በአናሳ ሥደተኞች የአህማዲ ማኅበረሰብ ይዞታ የሆነን አንድ የአምልኮ ሥፍራና አጠገቡ የሚገኙ የመኖሪያ ሰፈሮችን ማውደማቸው ተገለፀ።
አንድ የአህማዲን ማኅበረሰብ ቃል-አቀባይ ትናንት ማምሻውን ባስተላለፈው ቃል፣ ይህን ወደ 6መቶ ያህል ወንበዴዎች ተሳታፊዎች የሆኑበትንና በምሥራቃዊቷ ሲያልኮት ከተማ የደረሰውን ጥቃት አውግዞ፣ ውድመት የደረሰበት የአምልኮ ሥፍራ የመቶ ዓመት ዕድሜ ያለው እንደሆነም ገልጿል።
የጥቃቱን አፈፃፀም የሚያመለክት በተንቀሳቃሽ የእጅ ስልክ ላይ የተቀረፀ ምስልም ይፋ መሆኑ ታውቋል።
የወደሙት ህንፃዎች ከታሪካዊነታቸው በቀር፣ ድርጊቱ በተፈፀመበት ወቅት ባዶ ስለነበሩ፣ በሰው ሕይወት ላይ የደረሰ ጉዳት እንደሌለም፣ ቃል አቀባዩ ለቪኦኤ ገልጿል።