አጥፍቶ ጠፊዎች ሰሜናዊ ሊብያ ውስጥ በሚገኝ የነዳጅ ማውጫ ተቋም ላይ ጥቃት ማድረሣቸው ተገለፀ

ጥቃቱ ያነጣጠረው ነዳጅ ወደ ውጭ ሃገር የሚልከውን አል-ሲድራ ተቋም ሲሆን በፈጠረው ሁኔታ ሁለት ወታደሮች መገደላቸውም ታውቋል፡፡

እሥላማዊ መንግሥት ነኝ የሚለው ቡድን አጥፍቶ ጠፊዎች ሰሜናዊ ሊብያ ውስጥ በሚገኝ አንድ የነዳጅ ማውጫ ተቋም ላይ ዛሬ፤ ሰኞ ጥቃት ማድረሣቸው ተገለፀ፡፡

ይሁንና አጥቂዎቹ በቶሎ መባረራቸውን የጦር ኃይል ባለሥልጣናት አስታውቀዋል፡፡

ጥቃቱ ያነጣጠረው ነዳጅ ወደ ውጭ ሃገር የሚልከውን አል-ሲድራ ተቋም ሲሆን በፈጠረው ሁኔታ ሁለት ወታደሮች መገደላቸውም ታውቋል፡፡

አይሲል ባሠራጨው የትዊተር መልዕክቱ ተዋጊዎቹ በአል ሲድራ ተቋም ላይ ጥቃት ያሄዱት “የግዜር ጠላቶች” በሚላቸው ኃይሎች ላይ በጀመረው ዘመቻ መሠረት መሆኑን ገልጿል፡፡ የዜና ዘገባችንን ከድምጽ ፋይሉ ያዳምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

አጥፍቶ ጠፊዎች ሰሜናዊ ሊብያ ውስጥ በሚገኝ የነዳጅ ማውጫ ተቋም ላይ ጥቃት ማድረሣቸው ተገለፀ