እሥልምና በኢትዮጵያ፤ የዛሬ ጉዳዮች፣ አስተሣሰቦችና ግንኙነቶች

የሙስሊሙ ጥያቄዎች ምንድናቸው? አግባብነታቸውና ሕጋዊነታቸው ምን ይመስላል? መንግሥት መልስ ሰጥቻለሁ ይላል፤ አስተባባሪዎቹ አልተመለሰልንም ይላሉ፡፡ የአክራሪነት መሠረቶችና መገለጫዎች በኢትዮጵያ አሉ?

በኢትዮጵያ ሙስሊሙ ማኅበረሰብ ያነሣቸውን ጥያቄዎች፣ የጥያቄዎቹን አያያዝና ሌሎችም ተዛማጅ ጉዳዮችን እያነሣን የተለያዩ ዘገባዎችን በማቅረብ ላይ ነን፡፡

ባለፉ ጥቂት ወራት የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ የሆኑ ሙስሊሞች እያነሷቸው ያሉ ባለሦስት ነጥብ ጥያቄዎች አሉ፡፡

እነዚህም፡- አንደኛ የሙስሊሙ አመራር በሙስሊሙ የተመረጠ ይሁን፤ ሁለተኛ አህባሽ የሚባለውን አስተሣሰብ በኃይል ለመጫን እየተደረገ ያለው ግፊት ይቁም፤ ሦስተኛ የሙስሊሙ ተቋም አወሊያ በሙስሊም ምሁራንና በቦርድ ይመራ የሚሉ ናቸው፡፡

ቪኦኤ እያስተላለፈ ባሉ ዝግጅቶች የእሥልምና ታሪክ በኢትዮጵያ፤ የዛሬ ጉዳዮች፣ አስተሣሰቦችና ግንኙነቶች፤ እንዲሁም የወደፊት አቅጣጫና የመፍትሔ ሃሣቦች በተከታታይ ይቀርባሉ፡፡

በዚህ ዝግጅት እሥልምና ዛሬ ያለበትን ሁኔታ፣ የሙስሊሙን ጥያቄዎች፣ አክራሪነት በኢትዮጵያ ይኖር እንደሆነ በመጠኑ ለመዳሰስ እንሞክራለን፡፡

ምዕራፍ ሁለት

“እሥልምና በኢትዮጵያ፤ የዛሬ ጉዳዮች፣ አስተሣሰቦችና ግንኙነቶች”

ተንታኞቹ ፀሐፊ፣ ጋዜጠኛና የታሪክ ሰው ተሾመ ብርሃኑ ከማልና የሙስሊሙ ማኅበረሰብ ጥያቄዎች መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ አባሉ አቶ ከሚል ሸምሱ በዝግጅቱ ውስጥ ይናገራሉ፡፡

ያዳምጡት

(ገፁ ሲከፈት የተደራረቡ ወይም የተረበሹ ድምፆችን የሚሰሙ ከሆነ ከማጫወቻዎቹ አንደኛውን ብቻ አስቀርተው የቀሩትን ያቁሟቸው፡፡)