የአፍሪቃ ኮማንድ እዝ መሰረቱ ሶርያ የሆነው እስላማዊ መንግስት ነኝ የሚለው ቡድን በአፍሪቃ እየተስፋፋ መሄዱ አሳሳቢ ነው ብለዋል።
ዋሽንግተን ዲሲ —
መሰረቱ ሶርያ የሆነው እስላማዊ መንግስት ነኝ የሚለው ቡድን አፍሪቃ ድረስ እንደሰፋ የዩናትድ ስቴትስ (United States) የአፍሪቃ ኮማንድ እዝ ዋና ሃላፊ ተናግረዋል። ከናይጀርያ እስከ ሶማልያ ያሉትን ጽንፈኛ ቡድኖችን በመያዝ ወደ አውሮጳ ቅርበት ያለው ማዕከል እየመሰረተ ነው ሲሉም አክለዋል።
ጽንፈኛው ቡድን ስርት በተባለችው የሊብያ ከተማና አከባቢዋ 2,000 አማጽያን እንዳሉት የአፍሪቃ ኮማንድ ወይም እዝ የወታደራዊ እንቅሳቃሴ ምክትል ሃላፊ፣ ምክትል አድሚራል ማይክል ፍራንከን ገልጸዋል።
“ከሊብያ ወደ አውሮፓ መድረሱ በሚያሳስብ ሁኔታ ቀላል ነው” ሲሉ ማይክል ኦሃለን (Michael O’Hanlon) የተባሉ የመከላከያ ፖሊስ ጠቢብ አስገንዝበዋል። የዜና ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያዳምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5