የእስራኤል የመከላከያ ሚኒስትር አቪግዶር ሊበርማን በዛሬው ዕለት የሥራ መልቀቂያ አቀረቡ። ምክንያቱ ሀገራቸው ከፍልስጤሙ ነውጠኝ ቡድን ከሃማስ ጋር የደረሰችው የተኩስ አቁም ሥምምነት መሆኑ ተገልጿል።
ዋሺንግተን ዲሲ —
የእስራኤል የመከላከያ ሚኒስትር አቪግዶር ሊበርማን በዛሬው ዕለት የሥራ መልቀቂያ አቀረቡ። ምክንያቱ ሀገራቸው ከፍልስጤሙ ነውጠኝ ቡድን ከሃማስ ጋር የደረሰችው የተኩስ አቁም ሥምምነት መሆኑ ተገልጿል።
በግብጽ ሸምጋይነት የተደረሰውን ተኩስ አቁም ሥምምነት ሊበርማንና ሌሎችም በእስራኤል መንግሥት ውስጥ ያሉ ባለሥልጣናትና ሌሎችም ተቃውመውታል። ከዚያ ይልቅ የሚሻለው የእስራኤል ኃይሎች ጋዛ ሰርጥ ላይ የሃማስን ታጣቂዎች ደህና አድርገው ቢመቷቸው ነው ባዮች ናቸው።
የመከላከያ ሚኒስትሩ የተደረገው ውል ለሽብርተኛ እጅ ከመስጠት ይቆጠራል ብለዋል። ከዚህ ጥቂት ቀደም ብለው ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ጋዛ ላይ የሚካሄደውን ጥቃት እንዲቆም ስላደረጉበት ውሳኔያቸው ትክክለኝነት ተሟግተዋል። ጠላቶቻችን የተኩስ አቁም ያለህ ብለው ለምነውናል። ምክንያቱንም ያውቁታል ብለዋል ኔታንያሁ።