የእስላማዊ መንግሥት ቡድን (አይኤስ) መሪ አቡ በከር አል ባግዳዲ ወንድ ልጅ ሞራብ ሶሪያዋ ሆምስ ከተማ በአጥፍቶ ጠፊ ተልዕኮ ላይ ሞቷል የሚሉ ዘገባዎች ወጥተዋል።
ዋሺንግተን ዲሲ —
የእስላማዊ መንግሥት ቡድን (አይኤስ) መሪ አቡ በከር አል ባግዳዲ ወንድ ልጅ ሞራብ ሶሪያዋ ሆምስ ከተማ በአጥፍቶ ጠፊ ተልዕኮ ላይ ሞቷል የሚሉ ዘገባዎች ወጥተዋል።
የአይኤስ የዜና አውታር አል ናሺር የአልባግዳዲ ልጅ ሁዴይፋ አል ባድሪ ነው የተባለ የወጣት ልጅ ፎቶ አውጥቷል። ልጁ ሆምስ ውስጥ ከሩስያ እና ከሶሪያ መንግሥት ኃይሎች ጋር ሲዋጋ ሞቷል ብሏል።
የዩናይትድ ስቴትስ የጦር ሰራዊት ዘገባውን ኣንዳየው ገልፆ የአልባግዳዲ ልጅ መሆኑን ግን ከማረጋገጥ ተቆጥቧል።