በዚህ እለት የድምፅ ማጉያ ማይክራፎን ይዞ “Down Down Woyane” በሚል ተቃውሞ ሲያሰማ የነበረው ወጣት “በዕለቱ ከእኔ በስተቀር ማይክ ይዞ የተቃወመ የለም እኔ የምገኘውም በስደት ነው ብሏል”
ዋሽንግተን ዲሲ —
በቢሾፍቱ ሆራ አርሰዲ ኃይቅ በመስከረም 22/2009 ዓ.ም ሊከበር በዝግጅት ላይ የነበረውና ከኦሮሞ ክብረ በዓሎች አንዱ በኾነው እሬቻ በዓል ላይ ለደረሰ 55 ሰዎች ሕይወት መጥፋት ምክኒያት ናቸው የተባሉ ሁለት ሰዎች በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አራተኛ ወንጀል ችሎት ክስ ተመስርቶባቸዋል።
በእስር ላይ የሚገኙት ሁለቱ ተከሳሾች ክሱ የቀረበባቸው በዕለቱ የሀገር ሽማግሌዎች ንግግር ሲያደርጉ ማይክ በመቀማትና ሁከትና ብጥብጥ በመፍጠር በዓሉን አደናቅፈዋል ተብሎ ነው።
በዚህ ዕለት የድምፅ ማጉያ (ማይክራፎን) ይዞ “Down Down woyane” በሚል ተቃውሞ ሲያሰማ የነበረው ወጣት “በዕለቱ ከእኔ በስተቀር ማይክ ይዞ የተቃወመ የለም እኔ የምገኘውም በስደት ነው ብሏል”
ጽዮን ግርማ ዝርዝር አላት።
Your browser doesn’t support HTML5