የኢራቅ መንግሥት ኃይሎች ከሶሪያ ጋር በሚያዋስነው በረሃማ አካባቢ የቀሩትን “የእስልማዊ መንግሥት ነኝ” ባዩ ቡድን ተዋጊዎች ለማጥፋት ዛሬ ጥቃት ማካሄዳቸውን የሀገሪቱ ባለሥልጣናት አስታወቁ።
ዋሺንግተን ዲሲ —
የኢራቅ መንግሥት ኃይሎች ከሶሪያ ጋር በሚያዋስነው በረሃማ አካባቢ የቀሩትን “የእስልማዊ መንግሥት ነኝ” ባዩ ቡድን ተዋጊዎች ለማጥፋት ዛሬ ጥቃት ማካሄዳቸውን የሀገሪቱ ባለሥልጣናት አስታወቁ።
ጦር ሰራዊቱ ባወጣው መግለጫ የኢራቅ ጦር ሰራዊትና የሺያዎች ሕዝባዊ እንቅስቃሴ ኃይሎች ተዋጊዎች ስፋት ባለው የድንበሩ አካባቢ የቀሩትን የአይሲስ ርዝራዦች መንጥሮ ለማጥፋት በተከፈተው ዘምቻ መካፈላቸውን አመልክቷል።
የኢራቅ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይደር አል ኣባዲ ማክሰኞ ዕለት በሰጡት መግለጫ ቡድኑ በውጊያው ተሸንፉል፣ ነገር ግን ከበረሃው ውስጥ ጨርሾ ሳይወገድ ድል አድርገናል ብለን አናውጅም ማለታቸው ይታወሳል።